የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የቤንቶኒቴ ማእድን ማውጫ እና ማምረቻን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

October 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፋር ክልል ዋርሰሶ ወረዳ የቤንቶኒቴ ማእድን ማውጫ እና ማምረቻን ጎብኝተዋል::

ቤንቶኒቴ ለሴራሚክ እና ቀለም ብሎም ለመሰል ምርቶች ጠቀሜታ በመዋሉ “ትንግርታዊ ርጥብ አፈር” እና “ብዝሃ ጥቅም ያለው ሸክላ አፈር” በመባል በአድናቆት የሚነሳ ሃብት መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአፋር ክልል የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመጎብኘት ላይ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡