የሀገር ውስጥ ዜና

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ399 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

By Mikias Ayele

October 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 399 ሚሊየን 60 ሺህ ብር ድጋፍ ተደረገ፡፡

የኦሮሚያ ክልል 100፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 60፣ የአማራ ክልል 30፣ የሲዳማ ክልል 20 እና የሶማሌ ክልል 20 ሚሊየን ብር እና ሌሎች አካላትም ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን ለማልማት መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን ለማድረግም በጋራ መሥራት ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ቀጣዩ ሥራ ሕዝቡን አስተባብሮ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን መፍታት መሆኑን ጠቁመው÷ ለዚህ ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የሁላችንም እጣ ፈንታ በአንድ የተገመደ ነው ያሉት አቶ ሽመልስ÷ በትንንሽ ጉዳዮች እጅ ሳንሰጥ በጋራ ትልቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት መሥራት ይገባልም ነው ያሉት።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በበኩላቸው÷ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መመለሱ በተለያዩ ቦታዎች ከሕግ አግባብ ውጪ ፍላጎትን በጉልበት ለማስፈፀም ለሚንቀሳቀሱ አካላት ትልቅ ትምህርት የሰጠ ነው ብለዋል፡፡

በበረከት ተካልኝ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!