አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ባለፉት ሦስት ወራት ከ1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር መከናወኑ ተመላከተ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2016 (2023/24) በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባዔው እንደተገለጸው÷ ባለፉት ሦስት ወራት አበረታች የዲጂታል የባንክ አገልግሎት የሥራ አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡
በባንኩ ዲጂታል አማራጮች በተከናወኑ ከ245 ሚሊየን በላይ የገንዘብ ዝውወሮች ከ1 ነጥብ 3 ትሪሊየን በላይ የሆነ የብር መጠን መንቀሳቀሱን የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡