የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የንኢሌ ፓልም ስፕሪንግ ሎጅ ፕሮጀክትን አስጀመሩ

By Tamrat Bishaw

October 28, 2023

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ሥራ አካል የሆነውን የንኢሌ ፓልም ስፕሪንግ ሎጅ ፕሮጀክትን አስጀመሩ።

ፕሮጀክቱ በአፋር ክልል የሚገነባ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ይህ ስራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀመሯቸው እና ካከናወኗቸው የገበታ መርሐ ግብሮች በሶስተኛው ሊገነቡ ከታቀዱ ሰባት የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዱ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።