የሀገር ውስጥ ዜና

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

By Shambel Mihret

October 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ በሐዋሳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

የምክር ቤቱ ጉባዔ ለአንድ ቀን የሚካሄድ ሲሆን÷በሶሰት የተለያዩ አጃንዳዎች ላይ እንደሚወያይ ተገልጿል።

በጉባዔው ሞሽን ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የስራ ሃላፊዎች ሹመትን ለምክር ቤቱ አቅርበው ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም የምክር ቤቱ አባላት የሕግ ከለላ ስለማንሳት ላይ ተወያይተው ውሳኔ ይሰጣሉ መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።