አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (ግሎባል አሊያንስ) ለጤና ሚኒስቴር 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብቶችን ድጋፍ አደረገ፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ ቫይረሱን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
የድጋፍ ኮሚቴው አስተባባሪ የሆኑት አቶ አምሃ መኮንን በበኩላቸው የተደረገው ድጋፍ የፊት መሸፈኛ ማስኮች፣ ጓንቶች፣ የእጅ ንጽሕና መጠበቂያዎች፣ የመመርመሪያ መሳሪያዎችና ሌሎች የመከላከያ መሳሪያዎችም እንዳሉበት ገልፀዋል።
ድጋፉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።