የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አሸናፊዎች ታወቁ

By ዮሐንስ ደርበው

October 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የማሟያ ምርጫ አሸናፊዎች ታውቀዋል፡፡

በዚሁ መሠረት÷ ከትግራይ ክልል እግርኳስ ፌደሬሽን የተወከሉት ኮሎኔል አወል አብዱራሂም በ92 ድምፅ መመረጣቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም ከአፋር ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ኢብራሂም ሙክታር በ80 ድምፅ እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ማዕረጉ ሀብተማርያም በ76 ድምፅ ተመርጠዋል፡፡