አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በሀንሩካ ወረዳ በ220 ሄክታር ላይ እየለማ የሚገኘውን የሙዝ እና የፓፓያ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ያለንን መሬት ከአዋሽ ወንዝ ጋር በማስተሣሠር በሀገራችን የምግብ እጥረት የመቀነስ ሥራን ከግብ ለማድረስ በትጋት እንሠራለን ብለዋል።
በሀንሩካ ወረዳ በዚህ ዓመት በ220 ሄክታር የሙዝ እና የፓፓያ ምርት የተጀመረ ሲሆን÷ በተጨማሪ በቀጣይ ለሚሠሩ ልማቶች መሬት የማስተካከል ሥራዎች መከናወናቸው ተገልጿል፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉ የወረዳ አመራሮች ከዚህ የሥራ ልምድ በመነሳት የተጀመሩ ልማቶች አጠናክረው እንዲቀጥሉ ይረዳቸው ዘንድ አቅጣጫ አስቀምጠናል ብለዋል አቶ አወል፡፡
ከጉብኝቱ ጎን ለጎን የችግኝ ተከላ መርሐ- ግብር ማካሄዳቸውንም ነው ያመላከቱት፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!