አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመንደርና ክልልነት አስተሳሰብ ወጥተን በጋራ በመቆም ሀገራችንን ከጊዜያዊ ችግር በማላቀቅ ወደ ከፍታው ማማ ማውጣት ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ለሚ በዶ ገለጹ፡፡
የምክር ቤት አባላት በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ውጤቶችን ማበረታታትና ችግሮችንም ተወያይቶ የመፍታት ሀገራዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው ምክትል አፈ-ጉባዔዋ አስገንዝበዋል።
አባላቱ ለሀገሪቱ ዕድገት ማነቆ የሆኑ ሕጎችን፣ ደንቦችንና ፖሊሲዎችን በመፈተሽ የተሻለ ሥራ የመሥራትና ችግሮችን ለመፍታት የምክር ቤቱን ተልዕኮና ተግባራት መሠረት በማድረግ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙንም ሀገሪቱ እድገት ማስመዝገቧንና የተሻለ ሀብት የመፍጠር እንዲሁም የሀገራችንን ፀጋዎች የመጠቀም ዕድል እንዳለን በአግባቡ ተረድቶ መሥራት ያስፈልጋል ማለታቸውን የም/ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም የሀገሪቱን ዘላቂ ሠላምና ዕድገት ለማረጋገጥ የጋራ ባሕላችንን ማጎልበት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን ማሣደግ፣ የቁጠባ ባሕላችንን እና ያልተገባ የሀብት አጠቃቀማችንን መፈተሽ እና ማስተካከል ይገባል ብለዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በአፍሪካ አመራር ልኅቀት አካዳሚ ‹‹ከዕዳ ወደ ምንዳ›› በሚል መሪ ሐሳብ ስልጠና እየተከታተሉ እንደሚገኙ መገለጹ ይታወቃል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!