አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፐብሊክ ሰርቪስና ትራንስፖርት አገልግሎት የኢ- ቲኬቲንግ መተግበሪያን ይፋ አድርጓል።
አገልግሎቱ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት በቴክኖሎጂ ለማዘመን ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን የፐብሊክ ሰርቪስና ትራንስፖርት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ፍሬሕይወት ትልቁ ተናግረዋል፡፡
መተግበሪያው ደንበኞች ያለምንም መጉላላት ባሉበት ሆነው በተለያዩ አማራጮች ክፍያን በመፈፀም አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የተገልጋዩን ዕርካታ ለማረጋገጥና ከዕንግልት ለመታደግ ዘርፉን በቴክኖሎጂ መደገፍ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉን ዲጂታላይዝ የማድረጉ ሥራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ቀድሞ አሠራሩን በቴክኖሎጂ ማዘመኑን አድንቀው÷ በግሉ ዘርፍ የተሠማሩ መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሠራራቸውን እንዲያዘምኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ሀገር ለወጠነችው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የሥትራቴጂ ዕውን መሆን ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው አመላክተዋል፡፡
በወንድሙ አዱኛ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!