አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስተንሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ በግብርናው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በተለይም በዘላቂ ደን ልማት አስተዳደር ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት ላይ በትብብር በቅንጅት ለመስራት ተወያይተዋል፡፡
በተጨማሪም የዜጎችን ሕይወት ማሻሻል በሚያስችሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ግቦች ዙሪያ መምከራቸውን አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡