ስፓርት

አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ሥምምነት ፈጸሙ

By Feven Bishaw

November 03, 2023

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል።

አሰልጣኝ ገብረ መድህን በዛሬው ዕለት የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝነት ሥምምነት መፈጸማቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አሰልጣኙ ለአንድ ዓመት ውል በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፈው ኢትዮጵያ መድንን ክለብ ሳይለቁ ደርበው የሚሰሩ ይሆናል።