ስፓርት

ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሚያደርጓቸውን የሜዳ ጨዋታዎች ሞሮኮ ላይ ያከናውናሉ

By Feven Bishaw

November 03, 2023

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሚያደርጋቸውን ሁለት የሜዳ ጨዋታዎች ሞሮኮ ላይ እንደሚያከናውኑ ተገለፀ፡፡

የመጀመሪያው ጨዋታ ከሴራሊዮን ጋር ኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም እና ሁለተኛው ጨዋታ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ኅዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚደረግ ታውቋል፡፡

በዚህም ሁለቱም የማጣሪያ ጨዋታዎች በሞሮኮ አል ጀዲዳ ከተማ የሚገኘው ኤል አብዲ ስታዲየም እንደሚደረጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።