የሀገር ውስጥ ዜና

የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

By Feven Bishaw

November 03, 2023

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ አደረገ፡፡

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የሚቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡