የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ ከፊንላንድ ቀይመስቀል ቦርድ ሰብሳቢ ጋር መከሩ

By Feven Bishaw

November 03, 2023

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከፊንላንድ ቀይመስቀል ቦርድ ሰብሳቢ ኤሊ አልቶነን ጋር ተወያዩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ በውይይቱ÷ በኢትዮያና በፊንላንድ ቀይ መስቀል ድርጅቶች መካከል ያለው ግንኙነት 90 ዓመት ያስቆጠረና ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር መረጃ መሠረት በግጭቶችና የተፈጥሮ አደጋዎች በሚሊየኖች የሚቆጠር ሕዝብ በተለይም ሴቶችና ሕጻናት ድጋፍ የሚሹ በመሆኑ ድጋፉ እንዲጠናከር ፕሬዚዳንቷ ጠይቀዋል፡፡