የሀገር ውስጥ ዜና

ቼክ ሪፐብሊክ በውኃ ሐብት ልማት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር እየሠራች ነው – ሚኒስቴሩ

By ዮሐንስ ደርበው

November 04, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቼክ ሪፐብሊክ በኢትዮጵያ በከርሰ ምርድና በገጸ ምድር ውኃ ላይ ትኩረት ያደረጉ የጥናት ሥራዎች ላይ እየተሳተፈች መሆኗን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴርን ዛሬ ሲጎበኙ÷ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)ን ጨምሮ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም÷ ኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ  የከርሰ  ምድርን ውኃ በምርምር ጥቅም ላይ ማዋል (ሃይድሮጂኦሎጂ) ዙሪያ ለረጅም ጊዜ የቆየ ትብብር እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላት እምቅ ሐብትና እየተሠሩ ባሉ ሥራዎች ዙሪያ ገለጻ ተደርጎላቸው፡፡

ይህም በቀጣይ ሀገራቱ በውኃ ሐብት ላይ ያላቸውን ትብብር ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር መሰረት የሚጥል ነው

ኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ በውኃ ሐብት ልማት በተለይም በከርሰ ምድርና ገጸ ምድር ውኃ ጥናት ሥራዎች በትብበር እየሠሩ መሆናቸውንም ነው ሐብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) የተናገሩት፡፡

የቼክ ሪፐብሊክ መንግሥት በኢትዮጵያ 38 ሚሊየን ዩሮ በመመደብ በተለይም በሶማሌ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ እና አማራ ክልሎች የውኃ ሐብት ልማት ላይ እየሠራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!