ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና በራስ አቅም የሠራቻትን ግዙፍ መርከብ አስተዋወቀች

By ዮሐንስ ደርበው

November 04, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ የሠራቻት “አዶራ ማጂክ ሲቲ” የተሰኘች ግዙፍ መርከብ ለቀዘፋ መዘጋጀቷ ተሰምቷል፡፡

በዛሬው ዕለት በሻንግሃይ ለዕይታ የቀረበችው “አዶራ ማጂክ ሲቲ አንድ መለስተኛ መንደር” እንደማለት ነች ሲል ቻይና ዴይሊ ዘግቧል፡፡

323 ነጥብ 6 ሜትር ርዝመት ያላት መርከቧ÷ 135 ሺህ 500 ቶን የመጫን አቅም እንዳላት ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በአንድ ጊዜ 5 ሺህ 246 መንገደኞችን መጫን እንደምትችልም ነው የተመለከተው፡፡

“አዶራ ማጂክ ሲቲ” 2 ሺህ 125 የማረፊያ ክፍሎች እንዳሏት ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ግዙፏ መርከብ የመጀመሪያ የንግድ ጉዞዋን በፈረንጆቹ ጥር 1 ቀን 2024 እንደምትጀምር ተነግሯል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!