አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮግራም ምጣኔ ሃብትን ለማሳደግ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮግራም የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ መድረክ ተካሄዷል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ÷የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት እና የልማት አጋር ድርጅቶች ገበያ ተኮር ኩታ-ገጠም እርሻን ለማስፋፋት የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል፡፡
በመድኩ በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ግጭት በትግራይ ተቋርጦ የነበረው የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ስራ እንዲቀጥል በቅርቡ ለክልሉ የተደረገውን ድጋፍ የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ፕሮግራሙ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች እና በሲዳማ ክልሎች በ300 ወረዳዎች ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡