የሀገር ውስጥ ዜና

በሱዳን በጦርነት ቀጣና ውስጥ ያሉ ዜጎችን የማስወጣት ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ

By Feven Bishaw

November 06, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በተለያዩ ምክንያቶች ለመውጣት ያልቻሉትን እና ጦርነቱ በሚካሄድባቸው ቀጣና ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መንግሥት የማስወጣት ሥራ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ይህንኑ የማስወጣት ሥራ እያስተባበረ ያለው በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመው ግብረኃይል ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ተመላሾችን ያሳፈሩ አራት አውቶቡስ ከካርቱም ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ አድርጓል ነው የተባለው።

የተቋቋመው ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተመላሾች ወደ የቤተሰቦቻቸው እስከሚደርሱ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ መገለፁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከአሁን በፊት ከ34 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያውያን ከጦርነት ቀጣና ወጥተው ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡