የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ሚኒስቴርና የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ

By Melaku Gedif

November 06, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስቴር እና የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በማሪታይም ዘርፍና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በመረጃ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የውሃ ህግጋት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነውመባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሚኒስትሮቹ በሰጡት መግለጫ ስምምነቱን በአግባቡ ለመተግበር አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።