የሀገር ውስጥ ዜና

የትምሕርትን ጉዳይ “የኔ” ብሎ ሁሉም እንዲረባረብ ርዕሠ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ አሳሰቡ

By ዮሐንስ ደርበው

November 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምሕርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ ወራት ተግባራትን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጂንካ እየመከረ ነው፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ለሁሉም መሠረት የሆነውን ትምሕርት የኔ ጉዳይ ብሎ ሁሉም በርብርብ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምሕርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር)÷ ትምሕርት በዕውቀት፣ በክኅሎትና በሥነ- ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመፍጠር ዐይነተኛ ሚና ቢኖረውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘርፉ እየተመዘገበ ያለው ውጤት በቀጣይ ሰፊ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

በኢብራሂም ባዲ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!