የሀገር ውስጥ ዜና

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሽጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

By Feven Bishaw

November 07, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ)የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሽጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት ከጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል የተወሰነ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡