አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወጪ ፍላጎት በውስጥ ገቢ የሚሸፈንበት ሥርዓት መዘርጋት አለበት ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ተናገሩ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገቢና ፋይናንስ ዘርፎች የማስፈጸም ዐቅም ግንባታ የውይይት መድረክ በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የመንግሥት መዋቅሮች የወጪ ፍላጎት ከሚሰበስቡት ገቢና የውስጥ ዐቅም ጋር የሚጣጣምበት ሥርዓት መዘርጋት አለበት ብለዋል፡፡
የገቢ ምንጭ መሰረትን ማስፋትና የውስጥ ዐቅምን አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ገልጸው÷ የራስ ወጪ በውስጥ ገቢ መሸፈን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
ሕገ-ወጥ ንግድን መቆጣጠር፣ ደረሠኝ የመስጠት አሠራርን በተጠናከረ ሁኔታ መተግበርና አዳዲስ የገቢ አማራጮችን ማጥናትም ለገቢ ዕድገት ቁልፍ መሆናቸውን ነው በአጽንኦት የገለጹት፡፡
ለእነዚህ ሥራዎች ስኬትም የተደራጀና የተቀናጀ የአሠራር ሥርዓት ያስፈልጋል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
የግል ባለሀብቱ ኢንቨስትመንት በብዙ መልኩ ለገቢ ዕድገት ወሳኝ መሆኑንም አመላክተዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!