የሀገር ውስጥ ዜና

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ትምህርት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

November 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የትምህርት ሚኒስትር አህመድ ቤልሁ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በፓሪስ እየተካሄደ ከሚገኘው 42ኛው የዩኔስኮ ጠቅላላ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡

በዚህም የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የሰጠችውን ነጻ የትምህርት ዕድል፣ በዩኒቨርስቲዎች ራስ ገዝ አስተዳደር ተግባራዊነት እና በትምህርት መሰረት ልማት ዙሪያ መክረዋል፡፡

በቀጣይም የሁለቱ ሀገራት የትምህርት ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስትሮቹ በአዲስ አበባና በአቡዳቢ ተገናኝተው ለመወያየት መስማማታቸውን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia #UAE #France #UNESCO

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!