የሀገር ውስጥ ዜና

ንጋት ኮርፖሬት በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ20 ሚሊየን ብር የምግብ ድጋፍ አደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

November 10, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ንጋት ኮርፖሬት በአማራ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ20 ሚሊየን ብር የምግብ ድጋፍ አድርጓል።

ኮርፖሬቱ በ20 ሚሊዮን ብር 4 ሺህ 470 ኩንታል የምግብ ዱቄት ገዝቶ ለክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን ማስረከቡ ተመላክቷል።

ድጋፉ በሰሜን ጎንደር ዞን እና በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ነው ተብሏል።

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ፣ ጃናሞራ፣ ጠለምት፤ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰሃላ ሰየምት እና አበርገሌ ወረዳዎች በተደጋጋሚ ባጋጠመው የዝናብ እጥረት ወገኖች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው እና እስካሁንም ለ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ወገኖች መንግሥት ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!