ስፓርት

የ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የውድድር ዘመን ነገ ይጀመራል

By Tamrat Bishaw

November 10, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የውድድር ዘመን ነገ በሚደረጉ ስድስት ጨዋታዎች ጅማሮውን እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ዘንድሮ በሁለት ምድቦች 28 ክለቦችን ተሳታፊ የሚያደርገው ውድድሩ በሐዋሳ እና አዲስ አበባ የሚከናወን መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከውድድሩ ቀደም ብሎም በሁለቱም ምድቦች የውድድር አመራሮች እና ተሳታፊ ክለቦች የቅድመ ውድድር ስብሰባ ተከናውኗል።

ነገ በሚኖረው መርሐ ግብርም ከምድብ ሀ ጅማ አባ ጅፋር ከወልዲያ፣ ነቀምቴ ከተማ ከ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ፣ ንብ ከ ቤንች ማጂ ቡና በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በምድብ ለ ቢሾፍቱ ከተማ ከ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ ደሴ ከተማ ከ የካ ክ/ከተማ፣ ጋሞ ጨንቻ ከ ካፋ ቡና በሐዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡