የሀገር ውስጥ ዜና

የጉህዴን ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ሕብረተሰቡ ተመለሱ

By ዮሐንስ ደርበው

November 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዱራ ወረዳ በጫካ ውስጥ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጉህዴን ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ሕብረተሰቡ መመለሳቸውን የመተከል ዞን አስታወቀ፡፡

ታጣቂዎቹ የሰላም አማራጭን ተቀብለው ወደ ሕብረተሰቡ መመለሳቸው የቀጣናውን ሰላም በዘላቂነት የተረጋጋ እንዲሆን ያስችላል ሲሉ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለሜሳ ዋውያ ተናግረዋል፡፡

በተማሩበትና ፍላጎታቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት በተለያዩ ዘርፎች ለማሰማራት መንግስት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ወደ ሰላምና ልማት ለመግባትም በጉሙዝ ብሔረሰብ ባሕላዊ የእርቅ ሥነ- ሥርዓት መካሄዱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!