የሀገር ውስጥ ዜና

“ብቁ” መተግበሪ በቀን ከ2 ሺህ በላይ ዜጎችን የማሰማራት ዐቅም አለው ተባለ

By ዮሐንስ ደርበው

November 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት አገልገሎት የለማው “ብቁ” የተሰኘው መተግበሪያ በቀን ከ2 ሺህ በላይ ዜጎችን ለሥራ ማሰማራት የሚያስችል ዐቅም መፍጠሩ ተገለጸ፡፡

የውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪትን ፍትሐዊነት፣ ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃያት ካሚል ተናግረዋል፡፡

ለዘርፉ የሥራ ክንውን የሚያግዝ “ብቁ” የተሰኘ መተግበሪያ ለምቶ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸው÷ መተግበሪያው የዜጎች ደኅንነት ተጠብቆ እና በሕጋዊ መንገድ ብቻ ውል ፈፅሞ ለመሰማራት ያስችላል ብለዋል፡፡

በሀገር ውስጥ አምስት የሥራ ቋንቋዎችን ጨምሮ ሥድስት ዓለም አቀፍ ቋንቋዎችን ያካተተ ዘመናዊ መተግበሪያ በመሆኑ ዜጎች በቀላሉ መገልገል እየቻሉ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ከኢትዮጵያ ጋር ውል የገቡ ሀገራት ስምምነቶችን በአግባቡ እንዲተገብሩ የሚያስችልና አሠራርን ፍትሐዊ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የሚያደርግ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!