ዓለምአቀፋዊ ዜና

ጋናዊው አጥቂ ራፋኤል ድዋሜና በጨዋታ መሐል ሕይወቱ አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

November 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልባኒያ ሊግ ሲጫወት የነበረው ጋናዊው አጥቂ ራፋኢል ዳዋሜና ራሱን ስቶ ከወደቀ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን የአልባኒያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

የ28 ዓመቱ ራፋኤል ለአልባኒያ ሱፐርሊግ ተሳታፊው ኢግናቲያ ክለብ ከፓርቲዛኒ ጋር እየተጫወተ እያለ ነው ተዝለፍልፎ በወደቀበት ሕይወቱ ያለፈው፡፡

ተጫዋቹ ከዚህ በፊት ከልብ ሕመም ጋር በተያያዘ እግር ኳስ መጫወት እንዲያቆም ተነግሮት እንደነበር ቢ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

ድዋሜና በዘንድሮው የውድድር ዘመን በአልባኒያ ሊግ ዘጠኝ ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ተጫዋች ነበር፡፡

የወጣቱን አጥቂ ድንገተኛ ሕልፈት ተከትሎ በአልባኒያ ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎች ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፈዋል፡፡

የአልባኒያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተጫዋቹ ሕልፈት የተሰማውን ሐዘን ገልጾ÷ ለቤተሰቦቹ እና ለመላው ጋናውያን መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

ድዋሜና በ2017 ብራይተንን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ቢደርስም ከልብ ጋር በተያያዘ የሕክምና ምርመራውን ባለማለፉ ስምምነቱ መቋረጡ ይታወሳል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!