ስፓርት

አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ሲዳማ ቡና በይፋ ተለያዩ

By Melaku Gedif

November 13, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን ላለፈው አንድ ዓመት ሲያሰለጥን የቆየው አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ምክትላቸው ቾንቤ ገብረህይወት ከሲዳማ ቡና ጋር ተለያይተዋል።

የሲዳማ ቡና ዋና አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ምክትላቸው ቾንቤ ገብረህይወት ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየታቸውን የክለቡ መረጃ ያመላክታል፡፡

የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ቾንቤ ገብረህይወት በክለቡ በነበሩበት ወቅት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል፡፡