አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በመደበኛ ስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ያቀረቡትን የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ የሚሰጡ ይሆናል።
በዚሁ መሰረት የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ጥያቄና ማብራሪያ በማቅረብ ላይ ናቸው።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራሪያና ምላሽ ካደመጠ በኋላ ምክር ቤቱ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ የሐይማኖት አባቶች ተወካዮች፣ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ተጠሪዎች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።