የሀገር ውስጥ ዜና

የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከነገ ጀምሮ ይሰጣል

By Feven Bishaw

November 14, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ2ኛ ጊዜ ነገ እና ከነገ በስቲያ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ፈተናው በ46 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን ÷ 9 ሺህ 70 ተማሪዎች ለመፈተን መመዝገባቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህም ፈተናው ሕዳር 5 እና 6 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡