የሀገር ውስጥ ዜና

በቻይና ብሔራዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

By ዮሐንስ ደርበው

November 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ብሔራዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር ሎሳንግ ጂያልትሰን የተመራ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ አቀባበል አድርገውለታል።

ልዑኩ በቆይታው ከምክር ቤት አባላትና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል ሲል አዜአ ዘግቧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!