የሀገር ውስጥ ዜና

ከዘንድሮው የፀረ-ሙስና ቀን አከባበር ጎን ለጎን የተቋማት አመራር ኃላፊዎች ሃብት ምዝገባ ይካሄዳል

By Meseret Awoke

November 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው 20ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ከበዓሉ ሁነቶች ጎን ለጎን የተቋማት አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ሃብት ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የዘንድሮውን የፀረ ሙስና ቀንን በማስመልከት መግለጫ ሰጥቷል።

“ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል”በሚል መሪ ሀሳብ 20ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ከሕዳር 1 እስከ ሕዳር 25 ቀን እየተከበረ መሆኑ በመግለጫው ተገልጿል።

በዓለም ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሙስና አፈፃፀሙ እየረቀቀ፣ እየሰፋ በአስተዳደር እና በእድገት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑም ተመላክቷል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የፀረ ሙስና ትግሉን ተቋማዊ ቅርፅ እንዲኖረው አድርጋ መምራት ከጀመረች ሁለት አስርት ዓመታትን ማስቆጠሯም ነው የተገለጸው።

ሙስናን በቀጣይነት ለመከላከልም መንግስት የፀረ-ሙስና ትግሉ የተሟላ ቁመና እንዲኖረው ልዩ ልዩ የለውጥና የሕግ ማሻሻያ ስራዎችን በመስራት በሥነ-ምግባር ግንባታ፣ በሙስና መከላከል እና በሕግ ማስከበር ዙሪያ አዎንታዊ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ ተነስቷል።

በእለቱ ሙስናን ለመዋጋት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና የሚሰጥ ሲሆን ፥ ሕዳር 27 ደግሞ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የማጠቃለያ መርሐ- ግብር ይካሄዳል ነው የተባለው።

በሳሙኤል ወርቃየሁ እና ዙፋን ካሳሁን

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!