የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የኮሙኒኬሽንና መረጃ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ተሳተፈች

By Melaku Gedif

November 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ከበደ ዴሲሳ በ42ኛው የዩኔስኮ ጠቅላላ ጉባዔ የኮሙኒኬሽንና መረጃ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በጉባዔው የአባል ሀገራት የመረጃ ተደራሽነት፣ የብዘሃ ቋንቋ አጠቃቀም፣ የመረጃ ነፃነት፣ የዲጅታል ሚዲያ አጠቃቀም፣ ተደራሽነትና አስተዳደር አፈፃፀም ተገምግሟል።

በኢትዮጵያ ባለፉት ቅርብ ዓመታት የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት፣ የመረጃ ተደራሽነትን ከማረጋገጥና የብዘሃ ቋንቋ አጠቃቀምን በማሳደግ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት መቅረባቸው ተጠቁሟል፡፡

ጉባዔው በቀጣይ የመረጃ ነፃነትና ተደራሽነትን ለማሳደግ የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀምን ማሳለጥና መግራት ላይ የጋራ ውሳኔ ማሳለፉን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡