አዲሰ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኩዌት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡
አምባሳደር ሰዒድ መሃመድ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሀገሪቱ ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ሚሻል አል አሕመድ አል ጃባር አል ሳባህ አቅርበዋል፡፡
አምባሳደሩ በዚህ ወቅት÷ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት አድንቀው በቀጣይ ትብብሮችን ይበልጥ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
የኩዌት መንግስትም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ለሚያደርጉት ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ልዑል አልጋ ወራሹ፥ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላስተላፉት መልካም ምኞት አመስግነዋል፡፡
ኩዌት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡
አምባሳደሩ በኩዌት በሚኖራቸው ቆይታ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!