የሀገር ውስጥ ዜና

በፍትሃዊ የወደብ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ሴሚናር እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

November 17, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፍትሃዊ የወደብ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ሴሚናር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡

ሴሚናሩ ፍትሃዊ የወደብ አጠቃቀም ለአፍሪካ ቀንድ ለዘላቂ ሰላምና ልማት በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ሴሚናሩ የወደብ አጠቃቀም ጂኦፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የሕግ እና ዲፕሎማሲያዊ ምልከታ የሚንጸባረቅበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚደንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር)÷ዩኒቨርሲቲዎች ትክክለኛ የመፍትሄ አቅጣጫ አመላካች እንዲሆኑ ና የአካዳሚክ ነጻነታቸው እንዲጠበቅ ራስ ገዝ እንዲሆኑ የተጀመረውን ጥረት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በግንባር ቀደምትነት እየተገበረ ነው ብለዋል።

በመድረኩ የወደብ አጠቃቀም ከጂኦፖለቲካ ምልከታ አንጻር የሚተነትን መነሻ ጽሑፍ ቀርቧል።

በሴሚናሩ ሁለት ተጨማሪ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸውም ተመላክቷል፡፡

በምስክር ስናፍቅ