የሀገር ውስጥ ዜና

በላሊበላ ከተማ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

November 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ተፈጥሮ የነበረውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት በመፍታት ሰላም ለማስፈን ያለመ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ፣ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)፣ የሰሜን ምሥራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ሻምበል ፈረደ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳደሪ አራጌ ይመርን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡