አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ከተማ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የበጅግጅጋ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተጠቆመ ሚያረጋግጡ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ የከተማዋ ከንቲባ ዚያድ አብዲ (ኢ/ር) ገለጹ።
ከንቲባው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፥ ጅግጅጋ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአብሮነት የሚኖርባት እና ህብረ ብሔራዊነቷም ጎልቶ የሚታይ ከተማ ናት።
የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ያሉት ከንቲባው ፥ በመንገድ ግንባታ፣ በአገልግሎት መስጫ ፣ ከተማን በማስዋብና በአረንጓዴ ልማት አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።
በመንገድ ዘርፍ ከለውጡ በፊት ከነበረው 17 ኪሎ ሜትር የመንገድ ሽፋን አሁን ላይ ወደ 44 ኪሎ ሜትር ከፍ ማድረግ መቻሉንም ጠቁመዋል።
በሠላምና ፀጥታ ረገድ ቀድሞ የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ አስተማማኝ ሠላም መገንባቱን ነው የተናገሩት፡፡
ከዚህ ቀደም ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶች በማረፊያ ዕጦት ይቸገሩ እንደነበር ያስታወሱት ከንቲባው ፥ አሁን ላይ ከ30 በላይ ሆቴሎችና እንግዳ ማረፊያዎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ከተማዋ የንግድ ማዕከል መሆኗን ጠቁመው÷ይህንን ታሳቢ ያደረጉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስገንዝበዋል፡፡
የፊታችን ሕዳር 29 ለሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ከተማዋ እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቋም ተገልጿል።
በወንድሙ አዱኛ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!