የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮ-ጂቡቲ የመከላከያ ሚኒስቴር የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ተጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

November 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው ዙር የኢትዮ-ጂቡቲ የመከላከያ ሚኒስቴር የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በጂቡቲ እየተካሄደ በሚገኘው ስብሰባ ላይ ከኢትዮጵያ በኩል በብርጋዲየር ጄኔራል ተሾመ አናጋው የተመራ ልዑክ እየተሳተፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባው ጎን ለጎንም ብርጋዲየር ጄኔራል ተሾመ አናጋው ከጂቡቲ አቻቸው ብርጋዲየር ጄኔራል ጣሂር ዓሊ መሐመድ ጋር በጸጥታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ስብሰባው ነገ ፍጻሜውን ያገኛል መባሉን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!