አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል በአሸባሪው ቡድን ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሰበታ፣ ሃዋስና ቀርሳ ማሌማ በተባሉ አካባቢዎች ላይ በመንቀሳቀስ የህብረተሰቡን ሰላም ሲያውኩ በቆዩት የሽብር ቡድኑ አባላት ላይ ነው እርምጃ የተወሰደው፡፡
የክፍለ ጦሩ አዛዥ እንደገለፁት÷ ክፍሉ ሰሞኑን በወሰደው እርምጃ የጸረ-ሰላም ሃይሉ አመራር እና አባላት ተደምስሰዋል፡፡
የተለያዩ ዓይነት ጦር መሳሪያዎች እንደተማረኩ መናገራቸውንም ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም የሽብር ቡድኑ ሲጠቀምባቸው የነበሩ 8 ክላሽ፣ 350 የክላሽ ጥይት፣ 17 የክላሽ መጋዘን፣ 7 የወገብ ትጥቅና 1 ሽጉጥ መማረኩንም አንስተዋል፡፡
በዚህ ተልዕኮ አፈፃፀም በሽብር ቡድኑ እኩይ ተግባር የተሰቃየው የአካባቢው ማህበረሰብ የጠላት እንቅስቃሴን በመጠቆምና መንገድ በመምራት ለተልዕኮው መሳካት ያደረጉትን ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚመሰገን ነው ብለዋል።
በቀጣይም ማህበረሰቡ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም በሚወሰደው እርምጃ የተለመደውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡