ስፓርት

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ሩጫ የሰበረችው ክብረወሰን ፀደቀ

By Meseret Awoke

November 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ሩጫ የሰበረችው ክብረወሰን መጽደቁ ተነገረ፡፡

በአሜሪካ ኢውጅን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የዓለምን ክብረ ወሰን በመስበር ማሸነፏ ይታወሳል።

አትሌቷ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ሩጫ 14 ደቂቃ ከ00 ሴኮንድ ከ21 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት የርቀቱን የዓለም ክብረ ወሰን በእጇ አስገብታለች።

በዚህም አትሌቷ ያስመዘገበችው በዓለም ክብረወሰንነት መጽደቁን ከዓለም አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!