የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮ-አዘርባጃን ፓርላሜንታዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

By Shambel Mihret

November 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ፓርላሜንታዊ ግንኙነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ፡፡

ዛሬ በተካሄደው የጋራ መድረክ ÷ ሁለቱ ሀገራት በፓርላሜንታዊ ዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ እና በፐብሊክ ሰርቪስ ዘርፎች ግንኙነታቸውን አጠናክረው እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡

የኢትዮ- አዘርባጃን የፓርላማ የወዳጅነት ቡድን ሰብሳቢ ቤተልሔም ላቀው (ዶ/ር) ÷ ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር በንግድ፣ በትምህርት እና በኢንቨስትመንት አማራጮች በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮ-አዘርባጃን የፓርላማ ወዳጅነት ቡድን አባላትም ÷ የሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ሩስላን ናሲቦቭ በበኩላቸው ÷ ሁለቱ ሀገራት ፓርላሜንታዊ ግንኙነታቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ሀገራቱ በሁሉም መስክ ያላቸውን መልካም ተሞክሮና ልምድ በመለዋወጥ እድገት ማስመዝገብ እንዲችሉ በትኩረት እንሰራለንም ማለታቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

አዘርባጃን ለኢትዮጵያ ተማሪዎች በየዓመቱ የትምህርት እድል እየሰጠች እንደሆነም አምባሳደሩ በውይይቱ አንስተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!