አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ”ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው የመንግስት አመራሮች ስልጠና 4ኛው ዙር ዛሬ በተለያዩ ማዕከላት መሰጠት ጀምሯል።
በስልጠና መርሐ ግብሩ ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች የተወጣጡ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
ስልጠናው አመራሮች ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተገንዝበው ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ለሕዝቡ የተገባውን ቃል ማስፈፀም የሚያስችል አቅም እንዲፈጥሩ ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል፡፡
ስልጠናው በአመራሩ ዘንድ የተግባርና የሀሳብ አንድነት በማምጣት ሀገራዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅምና ክህሎት መፍጠር እንደሚያስችልም ተገልጿል፡፡
ከስልጠናው ጎን ለጎንም የልምድ ልውውጥ፣ የመስክ ምልከታዎች እና የተሞክሮ መቅሰሚያ መድረኮች በሁሉም ማዕከላት መዘገጀታቸውን የብልጽግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል፡፡
4ኛው ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ለተከታታይ አስራ ሁለት ቀናት የሚሰጥ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡