የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

By Feven Bishaw

November 25, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በሙሉ ድምጽ አጸደቀ፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

1-አቶ ጃንጥራር አባይ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

2-አቶ ጥራቱ በየነ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

3-ወ/ሮ ሂክማ ኬይረዲን የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ

4-ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ኃላፊ

5-ዶ/ር ጣሰው ገብሬ የፐብሊክ ሰርቪስ አና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

6-አቶ ሰለሞን አማረ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ

7-አቶ ተክሌ በዛብህ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ

8-አቶ አውራስ ከበደ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ኃላፊ

9-አቶ ሲሳይ ጌታቸው የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

10-ወ/ሮ ጽጌወይኒ ካሳ የቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ

11-ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን ኤኤምኤን ዘግቧል።