የሀገር ውስጥ ዜና

የፓን አፍሪካ ፖስታ ኅብረት ዋና ፀሐፊ የኢትዮጵያ ፖስታን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

November 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓን አፍሪካ ፖስታ ኅብረት ዋና ፀሐፊ ሲፉንዶ ቺፍ ሞዮ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፖስታን ጎብኝተዋል፡፡

ጉብኝቱ በየኢትዮጵያ ፖስታ እና በፓን አፍሪካ ፖስታ ኅብረት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና ሐሳብ ለመለዋወጥ ጠቃሚ ዕድል መስጠቱን የኢትዮጵያ ፖስታ አስታውቋል፡፡

በጉብኝታቸውም የኢትዮጵያ ፖስታን ዕድገት እና በቀጣይ በትብብር በሚከናወኑ ሥራዎች ላይ ከኢትዮጵያ ፖስታ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!