አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንኮራፋት በምንተኛበት ጊዜ በመተንፈሻ አካላችን ላይ በሚፈጠሩ ለውጦች ምክንያት የሚመጣ ድምፅ ነው።
ማንኮራፋት÷ አብሮ የሚተኛን ሰው ከመረበሽ ባለፈ አንዳንድ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጤና እክሎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
በእንቅልፍ ሠዓት ማንኮራፋትን ለመቀነስ የሚከተሉትን መፍትሄዎች ይከተሉ÷
1. የእንቅልፍ ሠዓትዎን ያስተካክሉ ÷ ለረጅም ሠዓታት ያለ ዕረፍት የሚሠሩ ከሆነ እና በመጨረሻ እጅግ በጣም እራስዎን ካዳከሙ የማንኮራፋት ድምፅ ያሰማሉ፤ ስለሆነም ለራስዎ በቂ ዕረፍት ይስጡ፤
2. ክብደትዎን ይቀንሱ ÷ ከጊዜ ወዲህ በመጣ ክብደት ማንኮራፋት የሚያስቸግርዎት ከሆነ ክብደትዎን በማስተካከል ማንኮራፋትን መቀነስ ይችላሉ፤
3. በጎንዎ ይተኙ ÷ በሚተኙበትን ወቅት በጀርባ ከመተኛት ይልቅ በጎንዎ መተኛት የአየር ቧንቧ መጥበብን በመከላከል ማንኮራፋትን መቀነስ ያስችልዎታል፤
4. ምቹ ትራስ ይጠቀሙ ÷ በሚተኙበት ወቅት እንደሁኔታው ለእርስዎ የሚመች ትራስ መጠቀም የማንኮራፋት ልምድዎን መቀነስ ያስችልዎታል፣
5. በቂ እንቅልፍ ያግኙ፣
6. አልኮል መጠጥ አይጠቀሙ ወይም በመጠኑ ያድርጉ ÷ የሚጠጡ ከሆነ ደግሞ ከመተኛትዎ በፊት ከ 2 እስከ 3 ሠዓታት አስቀድሞ መጠጣት፣ ይህም የበዛ የጡንቻ መላላት እንዳይኖር ይረዳል፤
7. ሲጋራ አያጪሱ፤
8. የአፍንጫ ቀዳዳዎችዎን በደንብ ያፅዱ፤
9. የአፍንጫ ወይም የመተንፈሻ አካል አላርጂክ ካለብዎ ሕክምና ይከታተሉ፤