የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

November 28, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)በቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ በይፋዊ አቀባበል ሥነ- ሥርዓት አቀባበል ተደርጎላቸዋል::

ሁለቱ መሪዎች ውይይት ያደረጉ ሲሆን÷ በውይይታቸውም በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር መወሰናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቼኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ባላፉት ቅርብ ሳምንታት ኢትዮጵያን በመጎብኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገው እንደነበር ይታወሳል።