አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም አቶ አወል የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እያከናወናቸው ስለሚገኙ የልማት ሥራዎችና ሌሎች ጉዳዮች ገለጻ አድርገዋል፡፡
አምባሳደሩ በአፋር ቆይታቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እንደሚጎበኙ የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ከተለያዩ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት እና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡