የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ወጣቶች ወር የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሄደ

By Shambel Mihret

November 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘንድሮ ለ16ኛ ጊዜ የተከበረው የአፍሪካ ወጣቶች ወር የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሄደ።

የማጠቃለያ መርሐ ግብሩ “ድንበር ተሻጋሪ የወጣቶች እንቅስቃሴ ለፓን-አፍሪካኒዝም“ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ እንደሚገኝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በየዓመቱ በፈረንጆቹ ህዳር ወር ሙሉውን የሚከበረው የአፍሪካ የወጣቶች ወር የአህጉሩን ወጣቶች ስብዕና ከመገንባት ጀምሮ ሌሎች ወጣቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቷቸው ውይይት ማድረግን ጨምሮ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል።

የአፍሪካ ወጣቶች ወር ሲከበር የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በተጨባጭ ለመተግበር የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ይመከራል።